በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው የኩርሙክ ወርቅ ማውጫን ጨምሮ በሌሎች ሀገራት የሚገኙ የወርቅ ማውጫዎችን የሚያስተዳድረው የካናዳው አላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽን እና የቻይናው ዚጂን ጎልድ ኢንተርናሽናል የግዢ ስምምነት መሰረዙ ተነግሯል።
የቻይናው ኩባንያ አላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽንን ሙሉ ለሙሉ ለመግዛት ከስምምነት ደርሶ የነበረ ቢሆንም ሁለቱ ኩባንያዎች ውልን በወቅቱ ለመፈጸም የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ባለመቻላቸው ስምምነቱ ተቋርጧል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን እና የኢትዮጵያ ትልቁ ዘመናዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ የሆነውን የኩርሙክ ወርቅ ማውጫን ጨምሮ በማሊ እና ኮትዲቯር የሚገኙ የወርቅ ማዕድናት በበላይነት የሚቆጣጠረው አላይድ ጎልድ እነዚህን የወርቅ ማውጫዎችን በ4 ቢሊዮን ዶላር ለመሸጥ አቅዶ ነበር፡፡
ነገር ግን ይህ ስምምነት በጋራ መግባባት መፍረሱን ተከትሎ በምትኩ ዚጂን ጎልድ 295 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት በአላይድ ጎልድ ላይ ለማድረግ ስለመስማማታቸው ነው የተነገረው፡፡
በዚህም መሠረት ዚጂን ማይኒንግ በአላይድ ጎልድ ውስጥ የ9 ነጥብ 2 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ይኖረዋል ነው የተባለው።
