የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይሄንን የገለጸው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን በገመገመበት ወቅት ነው።
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ከ38 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ለማምረት ታቅዶ ከ35 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል ማምረት ተችሏል ነው ያለው።
ይህም የዕቅዱን 93 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑንና ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመረተው ኃይል ጋር ሲነፃፀር የ21 በመቶ ዕድገት ያለው መሆኑን ገልጿል።
በበጀት ዓመቱ ከመነጨው ኃይል ውስጥ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 51 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም የጊቤ ሦስት እና የበለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የ17 ነጥብ 8 እና የ7 በመቶ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ተነስቷል።
