ቢቢሲ ከአንድ ከፍተኛ የሐማስ ባለስልጣን አገኘሁት ባለው ማረጋጋጫም ታጣቂ ቡድኑ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀረበውን ይህንን ትጥቅን ሙሉ ለሙሉ የመፍታት ዕቅድን መቀበሉን ነው ይፋ ያደረገው፡፡
እስራኤል ስለዚህ ጉዳይ እስካሁን በይፋ ያለችው ነገር ባይኖርም የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል ስምምነቱን አክብራ ወታደሮቿን ከጋዛ ሙሉ ለሙሉ ካላወጣች ፕሬዝዳንት ትራምፕ እጅግ እንደሚያዝኑባት ጠቁመዋል፡፡
ምንም እንኳን የዚህ ስምምነት መጨረሻ አሁን ላይ ባይታወቅም ሐማስ ከረጅም ጊዜ በኋላ ትጥቁን ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት ፈቃደኛ መሆኑ በራሱ ለጋዛ ሰላም አንድ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ እየተቆጠረም ይገኛል፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
