EthiopiaNews

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሀምሌ 16 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ከ704 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

ከተያዙት እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የቁም እንስሳት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒቶች እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል።

ከህገወጥ እቃዎቹ በተጨማሪ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የተገኙ 34 ተጠርጣሪዎች እና 14 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተጠቀሰው።

በዚህ ስራ የአዲስ አበባ ኤርፖርት፣ የአዋሽና የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ከፍተኛውን የኮንትሮባንድ እቃ በመያዝ ቀዳሚውን ስፍራ መያዛቸውም ተገልጿል።

ኮሚሽኑ ለተደረገው የጋራ ጥረት ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፣ የኮንትሮባንድ አፈጻጸም ስልት ተለዋዋጭ በመሆኑ ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv