የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ አውቶቡሶችን ወደ ተፈጥሯዊ ጋዝ የሚቀይር ቴክኖሎጂ መልማቱን አስታወቀ።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ይሄን ያሉት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ቢሾፍቱ ሞተር ቪየክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ባደረጉት ጎብኝት ላይ ነው።
ቢሾፍቱ ሞተር ቬሂክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ፍራንኩን ከተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ጋር በትብብር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶቡሶችን ወደ ተፈጥሯዊ ጋዝ መቀየር የሚያስችል ስራ እየሰራ ነው ተብሏል።
ሚኒስትር ዴኤታው ይህ በአፍሪካ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነው ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ መቀየሪያ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ እና ዘላቂ የትራንስፖርት ሥርዓት የምታደርገውን ሽግግር የሚያፋጥን ነው ብለዋል። መረጃው ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
