በ2018 በጀት ዓመት ከማዕድን ምርት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ባተኮረ የግምገማ መድረክ ላይ ነው።
የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ በበጀት አመቱ 44 ነጥብ 067 ቶን ወርቅ ማምረት ተችሏል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ከዚህ ውስጥ 40 ነጥብ 86 ቶን ያህሉ በባህላዊ ማዕድን አምራቾች የተመረተ መሆኑን ጠቅሰው ቀሪው 3 ነጥብ 209 ቶን ወርቅ ደግሞ በኩባንያዎች መመረቱን አብራርተዋል።
ሚኒስትሩ በዚህም ከወርቅ ምርት ከ5 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡መረጃው ከማእድን ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
