EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል መረቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር አዲሱ ተርሚናል ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ቀጥሎ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ትልቅ ተርሚናል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ተርሚናል ሰፊ የአውሮፕላን ማቆሚያዎችን፣ የላቁ መሰረተ ልማቶችን፣ የተስተካከሉ መዳረሻ መንገዶችን እና ዘመናዊ መገልገያዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲሱ ተርሚናል ምረቃ የአውሮፕላን ማረፊያውን የመቀበል አቅም በማሳደግ የአካባቢውን እያደገ የመጣ ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑን እና ለመንገደኞችም ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።

ይህ አዲስ ተርሚናል ከተማዋን እያደሰ ካለው የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ፤ ባህር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ሌላኛዋ ቁልፍ መዳረሻና ማዕከል ያደርጋታል ተብሏል።