የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ48 ሚሊዮን ደንበኞቹን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የ3ኛ ዙር የሳይበር ደህንነት ወር ንቅናቄ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
የባንኩ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት ምክትል ፕሬዚዳንት ሥዩም ዳምጠው በበጀት ዓመቱ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ የዲጂታል ግብይቶች መከናወናቸውን ጠቅሰው በእነዚህ ግብይቶችም ከ22 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚደርስ ገንዘብ መንቀሳቀሱን ገልጸዋል።
ይህ የግብይት መጠን የአገሪቱን 70 በመቶ የፋይናንስ ግብይት የሚሸፍን መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ይህንን የገንዘብ ዝውውር ከሳይበር አደጋዎች ለመጠበቅ በመጪው ጥቅምት የ3ኛ ዙር የሳይበር ደህንነት ወር ንቅናቄ እንደሚካሄድ አስረድተዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ንቅናቄ ባንኩ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር የዲጂታል ማጭበርበሮችን አስቀድሞ ለመለየትና ለመከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች እንደሚሰራም አክለው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ባንኩ በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚመጡ አዳዲስ የሳይበር ስጋቶችን ለመቋቋም የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል። በኬና ደሬሳ
Continue using AI Cursor?Keep it onTurn Off
