ኢትዮጵያ ዉስጥ የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ በደረሰዉ የአዉሮፕላን አደጋ ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ ቤተሰቦች የ29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደላቸዉ።
መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በቢሾፍቱ አጠገብ ወድቆ የተከሰከሰዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን አሳፍሯቸዉ የነበሩ 157 መንገደኞችና የአዉሮፕላኑ ሠራተኞች በሙሉ ህይወታቸው ማጣታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ አደጋ ህይወቱን ያጣው ማይክል ርያን ቤተሰቦች ናቸው ይህ ካሳ የተፈረደላቸው፡፡
የአሜሪካዉ አዉሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ለአደጋዉ ተጠያቂ መሆኑን ተከትሎ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች በድርድር ካሳ ሲክፈል የቆየ ሲሆን የማይክል ርያን ቤተሰቦች ጉዳዮን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰዳቸው ነው የቺካጎ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ካሳው እንዲከፈላቸው የወሰነው፡፡
