EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ “የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን በኦላይን ማሳወቅ እንደሚችሉ ገለጸ፡፡

ቢሮው ይሄን ያለው የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን ወደ ቅርንጫፎች በአካል መምጣት ሳይጠበቅባቸው በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ አማራጮች ባሉበት ክፍያ መፈፀም የሚያስችላቸው ስርዓት መዘርጋቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

የቢሮው የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ታዬ ማስረሻ የግብር ማሳወቂያና ክፍያ ወቅት ሲጀመር ግብር ከፋዮች በአካል ወደ ቢሮ ሳይመጡ አገልግሎቱን እንዲያገኙ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ኃላፊው ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ባለው የክፍያ ጊዜ ግብር ከፋዮች ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ፖርታል በቢሮው መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

ግብር ከፋዩ አመታዊ የሂሳብ መዝገቡን በአግባቡ በማዘጋጀትና ስካን በማድረግ በኦንላይን አመታዊ ግብራቸውንና የሂሳብ መዝገባቸውን ከስራ ቦታቸው በመሆን መላክ ይችላሉ ተብሏል። መረጃው ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የተገኘ ነው።