የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን አስታወቀ።
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔዎቹን ያስተላለፈው ዛሬ ባካሄደው የ6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።
ካቢኔው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መዋጮን ለማሻሻል እና በከፊል በኮሪደር ለምተው፣ በከፊል ሳይለሙ የቆዩ አካባቢዎችን በተሟላ ሁኔታ ለማልማት የቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦችን ተግባራዊ እንዲሆኑ አፅድቋል።
ካቢኔው ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች (ለሆቴል፣ ለሞልና አፓርትመንት፣ ኢንዱስትሪ፣ ለበጎ አድራጎት፣ መንግስታዊ ተቋማት እና የህክምና ተቋማት) የማስፋፍያና አዳዲስ የመሬት ጥያቄዎችን ለመመለስ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ተፈፃሚ እንዲሆን አፅድቋል።መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የተገኘ ነው።
