EthiopiaInternationalNews

ኢትዮጵያ ናይጄሪያው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ከሚያስገነቡት ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት ፍላጐት ማሳየቷ ተነገረ።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ዴቪድ ንዲ ይሄን ያሉት በናይኖቢ በተካሄደ መድረክ ላይ ነው።

ዳንጎቴ ኩባንያ በ16 ቢሊየን ዶላር ወጪ በኬንያ ከሚያስገነባው ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ 30 በመቶ የአክስዮን ድርሻ ለምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ለመሸጥ ይፋ አድርጓል ተብሏል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት አማካሪው ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለመሸጥ ይፋ ካደረገው የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር አክስዮኖች ውስጥ ኬንያ የ500 ሚሊየን ዶላር የአክስዮን ድርሻ ልትገዛ እንደምትችል ተናግረዋል።

አማካሪው ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በኬንያ ከሚገነባው የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ የአክስዮን ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት አሳይተዋል ብለዋል።

ዳንጎቴ በኬንያ በቀን 700 ሺ በርሜል ነዳጅ ማጣራት የሚችል ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ ለማስገንባት ከዚህ ቀደም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።ዘገባው የብሎምበርግ ነው።