EthiopiaNews

የሶላር ኃይል አቅርቦት ባላቸው አካባቢዎች ለአዲስ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ነፃ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ ግሪድ ርቀው በሚገኙና በፀሃይ ኃይል አማራጭ የኤሌክትሪክ አቅርቦት በተሰጣቸው አካባቢዎች ለሚገኙ አዲስ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ነፃ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለመግጠም አዲስ አሠራር መጀመሩን ነው የገለፀው፡፡

አሠራሩ በቅርቡ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ፣ ከሰኔ 2018 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 3 ሺህ 364 ደንበኞች በኦፍ-ግሪድ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ነፃ ቆጣሪ እንዲጠቀሙ ተደርጓል ነው የተባለው።

በዚሁ አሰራር እስከ አሁን 54 የሶላር ኃይል ማመንጫዎችን በመገንባት ከ11 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልጿል፡፡