EthiopiaNews

የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ አጠቃላይ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

የፋይናንስ አቅርቦት በተለይም የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ተያያዥ ችግሮች በግንባታው ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ መቆየቱን የገለጸው ተቋሙ አሁን ላይ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በራሱ በመሸፈኑ ግንባታው እየተፋጠነ እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡

የግድብ ግንባታውን በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ በማጠናቀቅ በጥቅምት 2021 ዓ.ም የመጀመሪያውን ተርባይን ወደ ኦፕሬሽን ለማስገባት እየተሠራ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡