EthiopiaNews

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልኡክ እና መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የ24 ሃገራት ኤምባሲዎች በኢትዮጵያ ሁሉም ወገኖች የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ገንቢ በሆነ መንገድ ለመተግበር ግንኙነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ኤምባሲዎቹ ይሄን ያሉት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጡት አጭር የጋራ መግለጫቸው ነው፡፡

በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በወቅታዊ ጉዳዮች ለመመምከር በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ያደረጉትን ጉብኝት እንደሚደግፉት ነው ሃገራቱ በጋራ መግለጫቸው ያስታወቁት።

ኤምባሲዎቹ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆነ ገልፀዋል።መረጃው ከኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልኡክ የተገኘ ነው።