የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 15 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱ ተነገረ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ይሄን ያለው በስሩ የሚገኙ ተቋማት አመታዊ አፈጻጸም ግምገማ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2018 በጀት አመት ያስገባው ገቢ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ60 በመቶ ጭማሬ እንዳለው ነው የተገለጸው፡፡
ባንኩ ለተለያዩ የሃገር ውስጥ ፕሮጀክቶች 20 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ማሰባሰብ መቻሉ ተገልጿል።መረጃው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተገኘ ነው።
