EthiopiaNews

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ፍትሃዊና ወጥነት ያለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመምህራን የደረጃ እድገት ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ይህ ተገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመከረበት ወቅት ሲሆን የመመሪያው መሻሻል ዋና ዓላማም አፈጻጸሙን ወጥ፣ ግልጽ፣ ዘላቂና ተራማጅ ማድረግ ነው ብሏል።

ከ2 ዓመት በፊት በሥራ ላይ የነበረው የቀድሞ መመሪያ 12 ሥርዓታዊና በርካታ የአተገባበር ችግሮች የነበሩበት እንዲሁም ለተለያዩ ትርጉሞች የተጋለጠ እንደነበር የጠቆመው ሚኒስቴሩ ማሻሻያው ይሄንን ክፍተት የሚሞላ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡