EthiopiaNews

ኢትዮጵያ የጉምሩክ እና የንግድ ስርዓቷን ለማዘመን እንዲሁም  የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደቷን ለማፋጠን እየሰራች መሆኗን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ታዜር ገብረእግዚአብሔር የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህንኑ የገለጹ ሲሆን ኢትዮጵያ ቀጠናዊ ውህደትን የልማት ስትራቴጂዋ አካል አድርጋ እየሰራች መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የቀጣናው ሀገራት የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው የምስራቅ አፍሪካ ኢንሼቲቭም ኢንቨስትመንቶችን ለማስተባበር፣ ፖሊሲዎችን ለማስማማት፣ ለንግድና ለግንኙነት እንቅፋት የሆኑ ማነቆዎችን ለመፍታት ወሳኝ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡