ትዮ ቴሌኮም በተያዘው የ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢውን 295 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱን ይፋ አደረገ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይሄን ያሉት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ኩባንያው በ2019 በጀት ዓመት አመታዊ ገቢውን 295 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱን ገልፀው ይህም ከቀዳሚው በጀት አመት አንጻር የ36 ነጥብ 7 በመቶ እድገት ያለው ነው ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በ2019 በጀት ዓመት 253 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መታቀዱን ነው ያስታወቁት።
በ2019 በጀት ዓመት በቴሌብር 7 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር ግብይት ይፈጸማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
