EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 አዲስ ዓመት የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስና ድንገተኛ ችግሮች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ በበዓላት ወቅት የሚያጋጥመውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ በመላ ሀገሪቱ በ2 ሺ 110 ኪ.ሜ የመካከለኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የፍተሻና የጥገና ሥራዎች በማከናወን ከ10 ሺ በላይ የኃይል መቆራረጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ግኝቶችን ሙሉ በሙሉ ማስተካከሉን ነው ያስታወቀው።

እንዲሁም ከ8 ሺ በላይ ትራንስፎርመሮች መፈተሻቸውን የጠቆመው አገልግሎቱ  በ6 ሺ 800 በላይ ትራንስፎርመሮች ላይ የተለዩ የቴክኒክ ችግሮች እንዲስተካከሉ መደረጉን ገልጿል፡፡

በበዓሉ ወቅትም የሚያጋጥሙ የኃይል ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ ለ24 ሰዓት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክ ቡድን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀት ወደ ሥራ መግባቱን አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv