EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግብ እያመራ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጳጉሜ 5 በሀገር አቀፍ ደረጃ የነገ ቀን በሚል መሰየሙን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ከወረቀት ወደ ዲጂታል የተደረገው ሽግግር ንግድና አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ፤ መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግና ዘርፎችንም የሚያዘምን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም ኢትዮጵያን በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን ያሳያል ነው ያሉት::

ያለፉት ቀናት ጳጉሜ 1- የእምርታ ቀን፣ ጳጉሜ 2-የማንሰራራት ቀን፣ ጳጉሜ 3- የጽናት ቀን፣ ጳጉሜ 4- የኅብር ቀን እንዲሁም ዛሬ የ2018ዓ.ም የመጨረሻ እለት ጳጉሜ 5- ደግሞ የነገው ቀን በሚል ተሰይመው በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መርሃግብሮች ተከብረዋል፡፡