EthiopiaNews

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል እና ጅግጅጋ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህክምና ሊሰጥ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ መሀመድ አያንሌ ይህ የህክምና ዘመቻ በተለይም የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ላለባቸውና የአይን ህክምና ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ነው ብለዋል።

ህክምናው ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነፃ የሚሰጥ በመሆኑ፣ የህክምና አገልግሎት ፈላጊዎች በህክምና ቡድኑ ለሚሰጠው አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑና እድሉን እንዲጠቀሙበት ሀላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ሰብአዊ ድጋፍ የተዘጋጀው በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ እና “አል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን” ከተባለው አለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተገልጿል።መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ