በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ያሉ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለፈው የ2018 በጀት ዓመት 500 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተነገረ።
ይህ የተነገረው በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን በገመገመበት መድረክ ላይ ነው።
በዚሁ ወቅት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለፈው የ2018 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 73 ትሪሊዮን ብር ገቢ ማግኘታቸው እንዲሁም ለመንግስት 367 ቢሊዮን ብር ግብር መክፈላቸው ነው የተነገረው።
