የአለም የጤና ድርጅት ከፈረንጆቹ 2026 እስከ 2027 ደረስ ለአፍሪካ 1 ነጥብ 13 ቢሊየን ዶላር በጀት መደቦ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
የአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና በእነዚህ ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ ሃገራት 1 ነጥብ 13 ቢሊየን ዶላር በጀት መድቦ እየተነቀሳቀሰ መሆኑን የገለጸው ከፈረንጆቹ 2028 እስከ 2029 ድረስ ለአፍሪካ ሊመድብ ያቀደውን በጀት በተመለከተ ባወጣው ሪፖርቱ ላይ ነው።
የአለም የጤና ድርጅት ከፈረንጆቹ 2028 እስከ 2029 ድረስ በአፍሪካ አገራት 1 ነጥብ 45 ቢሊየን ዶላር በጀት ለመመደብ ማቀዱን የገለጸ ሲሆን ይህም በእነዚህ አመታት ከፍተኛ በጀት ከመደበላቸው ቀጠናዎች ውስጥ አፍሪካ ግንባር ቀደም መሆኗም ተጠቁሟል።
