InternationalNews

የጌትስ ፋውንዴሽን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በዓለም ዙሪያ ተደራሽ እንዲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊመድብ መሆኑን አስታወቀ።

ፋውንዴሽኑ ባወጣው መግለጫ ከሚመደበው አንድ ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 40 በመቶ ለትምህርት፣ 40 በመቶ ለጤና፣ 10 በመቶ ለግብርና እና 10 በመቶ ለዲጂታል መሠረተ ልማት እንደሚውልም ገልጿል።

ፋውንዴሽኑ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲሰራ፣ የአካባቢዎችን ፍላጎት እንዲያሟላ እና ሰዎች ቴክኖሎጂውን በብቃት እንዲጠቀሙ ለማድረግ እንደሚሰራም አክሏል።

የጌትስ ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ቢል ጌትስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል ኩባንያዎች፣ መንግስታት እና የበጎ አድራጎት ተቋማት በጋራ መሥራት አለባቸውም ብለዋል።