EthiopiaNews

የታይላንድ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት አዲስ የቪዛ ስርአት ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ይፋ አደረገ።

የታይላንድ መንግስት ለበርካታ አገራት ሲሰጥ የቆየውን ያለቪዛ መግባት እና የመዳረሻ ቪዛ ተጠቃሚ የሆኑ አገራትን እንደገና በመከለስ ለተወሰኑ አገራት ብቻ እንዲሆን አድርጓል።

ቀደም ሲል ወደ ታይላንድ ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ሲሰጥ የነበረው የመዳረሻ ቪዛ ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በአዲስ የቪዛ ህግ የተተካ ሲሆን ይኸውም ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ከመነሳታቸው በፊት በOnline የመግቢያ ቪዛ thaievisa.go.th ላይ በማመልከት ሲፈቀድላቸው ብቻ መግባት እንደሚችሉ የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህን ተከትሎም በህንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው ማሳሰቢያ ከአሁን በኃላ ወደ ታይላንድ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ከመነሻው የታይላንድ ቪዛ ማግኘት እንደሚኖርባቸው ገልጿል።

መረጃው በህንድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ ነው።