አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ በ83 ዓመት እድሜያቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ግርማ ነጋሽ ምነው ተለየሺኝ፣ የኔ ሀሳብ፣ እንገናኛለን፣ አልበቃኝም ገና እና በሌሎች ተወዳጅ ዘፈኖቻቸው ይታወቃሉ፡፡
በአዲስ አበባ በ1936 ዓ.ም የተለዱት ድምጻዊው በፖሊስ ኦኬስትራና በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ በአሁኑ ብሔራዊ ቲአትር ለበርካታ አመታት በሙዚቃ ስራ አገልግለዋል፡፡
ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ የ3 ወንዶችና የ1 ሴት ልጅ አባት የነበሩ ሲሆን ስርዓተ ቀብራቸው ነገ ከቀኑ በ8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈፀማል ተብሏል፡፡
