InternationalNews

አሜሪካ ወታደራዊ ጫናዋን አቅልላ ወደቦቿ ላይ የጣለችውን እገዳ የምታነሳ ከሆነ፣ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን በሰባት ቀናት ውስጥ ለመክፈት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።

ለዚህም አሜሪካ ችግሩን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ያላትን ፍላጎት በይፋ በማሳወቅ፣ ለድርድሩ ግልፅ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ ልታስቀምጥ ይገባል ተብሏል።

በተመድ ጉባኤ ላይ የሚገኘው የኢራን ልዑክ ለድርድር ሙሉ ስልጣን ቢኖረውም፣ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ግን ከአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደማይገናኙ ተገልጿል።

አሜሪካ ሰላም ለማምጣት ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ ከፈለገች፣ አሁን እየተካሄደ ያለው የተመድ ጉባኤ ለዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ወርቃማ እድል እንደሚሆን ነው ቴህራን የገለጸችው ።

ይሁንና አሜሪካ አዲስ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀች ነው ያለው የኢራን ጦር፣ የትኛውም ጥቃት ቢሰነዘርብኝ የከፋ አፀፋዊ እርምጃ ከመውሰድ አልመለስም ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

በተመድ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው ግጭት በስምምነት ካልተቋጨ ኢራንን ሙሉ በሙሉ እንደሚያወድሟት ዝተዋል።