EthiopiaNews

ኢትዮጵያ፣ ብሪታንያ እና ኖርዌይ በአለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ ሊያስከትሉ የሚችሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የክትባት ምርምርና ልማትን ለሚደግፈው ሲኢፒአይ ተቋም 240 ሚሊየን ዶላር ለመለገስ ቃል ገቡ።

ሃገራቱ ለፕሮግራሙ ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡት በኒውዮርክ በመካሄድ ላይ ካለው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደ ውይይት ላይ ነው።

ድጋፉ ከፈረንጆቹ 2027 እስከ 2031 አመት ድረስ የሚተገበር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ኖርዌይ 106 ሚሊየን ዶላር፣ ብሪታንያ ድግሞ 134 ሚሊየን ዶላር እንደሚለግሱ ቃል ገብተዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ደህነንት ጉዳይ የሃገራት የጋራ ሃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለሲኢፒአይ ተቋም ድጋፍ እንደምታደርግም ተናገረዋል።