የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቅጠል ተራ 960 የመኖሪያ ቤቶች በአራት ወራት ውስጥ ተገንብተው ከቦታው ላይ ለተነሱ ነዋሪዎች መልሰው መተላለፋቸውን ተናገሩ።
ከንቲባዋ ቅጠል ተራ ቀደም ሲል እጅግ የተጨናነቀ፣ የተፋፈገና ለኑሮ ምቹ ያልነበረ አካባቢ እንደነበር እና በአካባቢው አስከፊ የእሳት አደጋ ተከስቶ የሰው ሕይወትም ጠፍቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
ከንቲባዋ አሁን ግን አካባቢው ” የመርካቶ የበጎነት መንደር ” በሚል ስያሜ ተሰይሞ፣ በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ ዘጠኝ G+8 ብሎኮችን ያካተተ መንደር መሆኑን ተናግረዋል።
ከንቲባዋ መንደሩ በአጠቃላይ 960 የመኖሪያ ቤቶች እና 371 የንግድ ሱቆችም ተገንብተውበታል ብለዋል።
ሱቆቹ ለነዋሪዎች የንግድና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር የሚያግዙ መሆናቸውን አዳነች ገልፀዋል።መረጃው ከአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የማህበራዊ ገፅ የተገኘ ነው።
