InternationalNews

በተያያዘ ዜና የኢፌዲሪ ርዕሰ ብሄር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲሻሻል ዳግም ጠይቀዋል።

በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ ብሄሩ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አጠቃላይ ማሻሻያ በማድረግ አፍሪካ ያጣችውን እኩል የመወከል መብት በአስቸኳይ ማስተካከል እንደሚገባው አሳስበዋል።

እንዲሁም 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ሕዝብ ያላት አፍሪካ እርሷን ባላሳተፈ ውሳኔ ስትመራ የቆየችበት ጊዜ ማብቃት እንዳለበት ገልጸው የይዘትና መዋቅር ማሻሻያው የትውልዶች ፍትሐዊ ጥያቄ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ የተመድ መሥራች አባል እንደመሆኗ መጠን፣ ለጋራ ደኅንነት የጸና እምነት አላት ያሉት ርዕሰ ብሄር ታዬ የባለብዙ ወገን ግንኙነት በሀገራት ሉዓላዊ እኩልነት ላይ የተመሠረተ የጋራ መጠለያ እንጂ፣ የዲፕሎማሲ ምቾት ብቻ ሊሆን እንደማይገባው አስገንዝበዋል።