የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በታያዘው የትምህርት ዓመት 10 ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስልጠን መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ኢንስቲትዩቱ አክሎም ከሚቀበላቸው ሰልጠኛች መካከል የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ይገኙበታል ብሏል።
ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ የሳይበር ደህንነትና በሌሎች አዳዲስ የሥልጠና መስኮችም ስልጠና መስጠት መጀመሩን ገልጿል።
የሰልጣኞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግም በቻይና ከሚገኙ የሥልጠና ተቋማት ጋር በትብብር የጣምራ ሰልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል መርሃ ግብር በመተግበር ላይ መሆኑን አመልክቷል።
ይኸው የጣምራ የሥልጠና መርሃ ግብር ሰልጣኞችን ወደ ቻይና በመላክ የተግባር የሥልጠና እንዲያገኙና ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ሚናው የጎላ ስለመሆኑ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ገልጿል፡፡
