EthiopiaNews

በመጪዎቹ ቀናት የሚከብሩት የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው የፊታችን መስከረም 16 ቀን የሚከበረውን በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል እንዲሁም መስከረም 23 ቀን በመዲናዋ የሚከበረውን የገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልከቷል።

በዓላቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲያልፉ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከጸጥታ አካላት እና ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይቶች መደረጋቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡