የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አዳዲስ የፓርላማ ተመራጭ አባላት በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡
አዲሱ የመንግሥት ምሥረታ እና የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በመጪው መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከናወን የገለጸው ምክር ቤቱ አዳዲስ ተመራጭ አባላት በመጪው መስከረም 21 ከጠዋቱ 2 ሰአት 30 ጀምሮ በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡
በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ የጠቀሰው ምክር ቤቱ የመንግሥት ምስረታ እና የምክር ቤቱ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ለማከናወን አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁ መገለጽም አይዘነጋም፡፡
