ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ተጠባባቂ የሆኑ ተማሪዎች በሙሉ ዛሬ እና ነገ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ተጠባባቂ ለሆኑ ተማሪዎች ባወጣው ማስታወቂያ ነው።
ሚኒስቴሩ ለፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ፈተና ወስደው ተጠባባቂ የሆኑ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 2 ተከታታይ ቀናት በተመዘገቡበት የምዝገባ ሊንክ በመግባት፣ ስማቸውን እና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እንዲመዘገቡ ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡
ሚኒስቴሩ ተጠባባቂ የሆኑ ተማሪዎች በዚህ 🔗 የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply ገብተው መመዝገብ ይችላሉ ብሏል።
መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
