InternationalNews

በሁለት የግድያ መርፌ የሞት ቅጣት የተፈፀመባት አሜሪካዊት እስረኛ ሕይወቷ ሳያልፍ ቀርቷል።

ክሪስታ ፓይክ የተባለችው ፍርደኛ በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት ትሙት በቃ ከተፈረደባት ከ30 ዓመታት በኋላ ትላንት በመርዝ እንድትገደል ሁለት መርፌ በተከታታይ ብትወጋም ልቧ ስራውን ባለማቆሙ ሕይወቷ ሊያልፍ አልቻለም።

የግድያ ሂደቱን ይከታተሉ የነበሩ ጠበቆችም የፍርድ አፈፃፀሙን ይከታተሉ ስለነበር ከተከታታዩ የመርፌ መወጋት ሂደት በኋላ ታንኮራፋ ነበር ብለዋል።

በዚህም ጠበቆቹ የግድያ ሂደቱ እንዲቆም በመጠየቃቸው ፍርደኛዋ ለህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።

ፓይክ ለሞት ፍርድ የበቃችው የ18 ዓመት ወጣት እያለች ፍቅረኛዬን ነጥቃኛለች በሚል የ19 ዓመቷን ኮሊን ስሌመርን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደሏ ነው።