የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ዘርፍ አጠቃላይ ሀብቱ 124 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገለጸ፡፡
ይህ የተባለው ትላንት መካሄድ የጀመረው ሁለተኛው ፋይናንስ ፎረም 2026 በዐድዋ ድል መታሰቢያ በዛሬው እለትም መካሄዱን በቀጠለበት ወቅት ሲሆን በመርኃግብሩ ዘርፉ የደረሰበት ደረጃ መልካም ጅማሮ ቢኖረውም ከዓለም አቀፍ እንዲሁም ከአፍሪካ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡
የኢንሹራንስ ዘርፉ ለውጥ እያሳየ መምጣቱን የገለፁት የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ አሶሴሽን ፕሬዝዳንት ያሬድ ሞላ በፈረንጆቹ 2026 መጨረሻ ድረስ ዘርፉ ተጨማሪ 54 ቢሊዮን ብር ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቅሰዋል፡፡
ባለፈው የበጀት ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ 13 ትሪሊዮን ብር ያህል የሚገመት ንብረት አደጋ ላይ እንደነበርም ፐሬዝዳንቱ በንግግራቸው ጠቅሰዋል፡፡
