EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢሬቻ በዓል ስናከብር እንደ እሴቱ አንድነትን አጥብቀን፣ እጃችንን ለሰላምና ለዕርቅ ዘርግተን፣ ቀልባችንን ወደ ይቅርታ መልሰን ስላገኘነው ነገር ፈጣሪን እያመሰገን ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ስልጣኔ ዕውን ለማድረግ ባለን ዕውቀት፣ አቅምና ሀብት ሁሉ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን በግንባር ቀደምነት ኢትዮጵያን እንድናፀና ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ፈተናዎች ቢኖሩም ለኢትዮጵያ መውጣት የጀመረው የለውጥ ብርሃን በየትኛውም የክረምት ጨለማ፣ ዶፍና ጭቃ ተንሸራትቶ ሊደናቀፍ አይችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንገድ ስተው ከሀገራቸው በተቃራኒ የቆሙ ዜጎች ፊታቸውን ወደ ሰላም ከመለሱ፤ የሰላም በር ክፍት መሆኑን ላረጋግጥ እወዳለሁም ብለዋል።

ኦሮሞ በትግሉ ነፃ ወጥቷል፤ ከዚህ በኋላ በጠብመንጃ አፈሙዝና ከጠላት ጋራ በመወገን የሚመለስ የኦሮሞ ጥያቄ አይኖርም ያሉት ዐቢይ አህመድ የኢሬቻን በዓል ስናከብር እንደ እሴቱ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡

በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡