EthiopiaNews

ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አሠራርን ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 8 አመታት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ዐቢይ አህመድን (ዶ/ር) ለቀጣይ የሥራ ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል።