በዓለም ዙሪያ የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ፍጥነት እየቀነሰ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ 2 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱ ተገልጿል።
እንደ ዓለም ባንክ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ከሆነ፣ ይህ ዕድገት ሀገሪቱን ከአፍሪካ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ አማካይ 0 ነጥብ 9 በመቶ በከፍተኛ ደረጃ ፈጣን የሕዝብ ዕድገት ካላቸው ሀገራት ተራ አድርጓታል።
በኢትዮጵያ የተመዘገበው ይህ ፈጣን የሕዝብ ዕድገት ሰፊ የሥራ ኃይል ዕድል የሚፈጥር ቢሆንም፣ በመሠረተ ልማት እና በማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ ጫና እንደሚያስከትል ተገልጿል።
በአንጻሩ በላቲን አሜሪካ የምትገኘው ዶሚኒካን ሪፐብሊክ የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ 0 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ደግሞ በ4 ነጥብ 7 በመቶ በዓለም ከፍተኛውን ዕድገት አስመዝግባለች።
እንደ ጃፓን እና አልባኒያ ያሉ ሀገራት ደግሞ የሕዝብ ቁጥር መቀነስ ያጋጠማቸው ሃገራት መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።
