EthiopiaNews

በአዲስ አበባ ከተማ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከትላንት መስከረም 28 እስከ ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ የከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።

ከጎሮ አደባባይ – ኮዬ ፈቼ – ቱሉ ዲምቱ አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ የኮሪደር መሰረተ ልማት እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው የተነገረው፡፡

በዚህ ምክንያትም  በሥፍራው እየተካሄደ የሚገኘውን የመንገድ መሠረተ-ልማት ማሻሻያ ከጎሮ ወደ ኮዬ ፈቼ በሚወስደው መንገድ ላይ በመሬት ውስጥ ለሚቀበሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ዝርጋታ ሲባል ዋናው አስፋልት መንገድ መቋረጡ ተገልጿል።

በመሆኑም ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በጎሮ – ቦሌ ኤርፖርት መንገድ አቅጣጫ ወደ ቡልቡላ ያለውን መንገድ እንዲጠቀሙ ነው የተጠቆመው፡፡

ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ደግሞ ከኮዬ ፈቼ አደባባይ – በቡልቡላ በኩል ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን የቦሌ ኤርፖርት – ጎሮ አዲሱን መንገድና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡