EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከነገ በስትያ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚጀምር አስታወቀ።

አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ደንበኞቹ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከላት በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉም ገልጿል።

መረጃው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘ ነው።