EthiopiaNews

ኢትዮጵያና ህንድ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት በማሳደግ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንት፣ በጤና፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች ትብብራቸው ለማስፋት እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የህንድና ኢትዮጵያ ግንኙነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1948 እንደሚጀምር ያነሱት በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የህንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር ባለፉት አስር አመታት ከ600 በላይ የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መሰማራታቸውንና ከ75 ሺህ በላይ የስራ እድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል።

ይህን ለማጠናከር እንደሚሰራ የገለጹት ሚኒስትሩ አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በቋሚና ተለዋጭ አባልነት ፍትሃዊ ውክልና ሊኖራት እንደሚገባም እነደሚሰሩም ጠቅሰዋል፡፡