EthiopiaNews

በአዲስ አበባ ከተማ 20 የነበሩትን የህጻናት ማቆያ ማዕከላት ወደ 1 ሺህ 200 ማሳደግ መቻሉን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ ገልጿል።

የከተማዋ ይህንን የገለጹት ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማንና ልዑካቸውን ጋር በነበራቸው ቆይታ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በዚሁ ወቅት ከንቲባዋ በከተማዋ በሕፃናት ላይ ትኩረት ተደርጎ የተጀመረው ፕሮግራም ሲጀመር 11 ብቻ የነበሩትን የሕፃናት መጫወቻ ሥፍራዎች በሦስት ዓመታት ውስጥ ወደ 6 ሺህ ማሳገድ ተችሏልም ነው ያሉት።

እንዲሁም በተሰሩት የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ሥራዎች፣ የእድገት ውስንነት የታየባቸውን ሕፃናት መጠን ዝቅ ማድረግ መቻሉም ነው የጠቀሱት።