EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ እና ሰላም የማስፈን ስራ እንደሚሰራ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት በክልሉ የተጎዳው ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማትን ለማነቃቃት ሊሰራ ይገባለ ነው ያሉት፡፡

በትግራይ ክልል ምርጫ ተደርጎ መደበኛ አስተዳደር እስኪመሰረት ድረስ የክልሉ ነዋሪዎች የመንግስት ተቋማትን እንዲጠብቁ እና ከፀጥታ አካላት ጋር ተባብረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የክልሉ ነዋሪዎች ወደ እርሻ፣ መስኖ፣ ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና የከተሞች ልማት እንዲመለሱ መልእክት አስተላልፈዋል።