EthiopiaNews

በትግራይ ክልል በመጪው ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሒደት እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመቐለ ከተማ የሚገኘውን አፄ ዮሐንስ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጎበኙበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው፡፡

በትምህርት ቤቱ ያለውን ሁኔታ ለመመልከትና መደበኛውን የመማር ማስተማር ሥራ ለማስጀመር የተደረጉ ዝግጅቶችን ለመገምገም በተደረገው በዚህ ጉብኝት የሥራ ኃላፊዎቹ ከመምህራን እና ከትምህርት ቤት አስተዳደር አካላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና በጉዳት ምክንያት የተቋረጠው የትምህርት አገልግሎት እንዲቀጥል ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ መምህራንና ተማሪዎች ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ በተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች በመገኘት ትምህርት ለመጀመር ዝግጁ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል የባለአደራ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች በመቐለና በኩይሃ ሆስፒታሎች በመገኘት የጤና ተቋማቱን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡