የኬንያ ፖሊስ ናይሮቢ ውስጥ ባንድ ቤት በተጎሳቆለ ሁኔታ ተይዘው የነበሩ 65 ኢትዮጵያዊያንን መታደጉን አስታወቀ።
ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ በሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በሞያሌ በኩል መግባታቸውን ለፖሊስ እንደተናገሩ ተገልጿል።
የኬንያ ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የተዛወሩ መሆኑን ገልፆ በሰው አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ ሦስት ኬንያዊያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑ በትክክል የሰው አዘዋዋሪዎች ወይም የሌላ ብዝበዛ ሰለባ መሆን አለመሆናቸውን እየመረመረ እንደሆነ ዘስታር ዘግቧል።
