ኢራን አሜሪካና እስራኤል ዳግም ጥቃት ከከፈቱብኝ በአሜሪካ ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እፈጽማለሁ ስትል አስጠነቀቀች፡፡
የኢራን የደህንነት ባለስልጣናት እንደገለጹት በእስራኤልና አሜሪካ ጥቃት የቴህራን አመራሮች ወይም ሲቪሎች ከተገደሉ በአሜሪካ ጥቅሞች ላይ ብቻ ሳይሆን ጦርነቱን በሚቀላቀሉ ሀገራት ላይ ጭምር ኢራን የበቀል ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅታለች፡፡
ኢራን አሜሪካና እስራኤል በጋራ በመሆን ዳግም ጥቃት ሊፈጽሙብኝ መዘጋጀታቸውን መረጃው ደርሶኛል ያለች ሲሆን አሜሪካ ግጭቱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ትፈታለች የሚለው ተስፋዬም ተሟጧል ብላለች፡፡
የኢራን ባለስልጣናት የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ፖሊሲ የሚመራው በእስራኤል በመሆኑ አሜሪካ ከቴህራን ጋር የገባችበትን ግጭት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት እንድትቸገር አድርጎታል ብለዋል፡፡
