InternationalNews

አሜሪካና እስራኤል ከአሜሪካ የምክር ቤት ምርጫ በኋላ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ለመፈጸም ዝርዝር ዕቅድ ማውጣታቸው ተገለፀ፡፡

ዘ ኒውዮርክ ታይምስ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው ወታደራዊ መረጃ መሰረት ሁለቱ ሀገራት በጋራ በመሆን ከምርጫው በኋላ በኢራን ላይ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እና እጅግ ከባድ የሆነ ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ይህንን ከባድ የተባለ ጥቃት በኢራን ላይ ለመፈጸም መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ እና ዝግጅት እያደረጉ ነው የተባለ ሲሆን ወታደራዊ ልምምዱም የኢራቅን የአየር ክልል ጭምር ያካታተ መሆኑም ነው የተሰማው፡፡

አሜሪካና እስራኤል በኢራን የኢነርጂ መሰረተ ልማቶች፣ የኒውክለር ጣብያዎች እንዲሁም የሚሳኤል እና ድሮን ማምረቻ ተቋማት ላይ ይህንን እጅግ ከባድ የተባለን ወታደራዊ ጥቃት ለመፈጸም መዘጋጀታቸውም ተገልጿል፡፡