ላለፉት 4 አመት ከ7 ወር ስራውን ሲሰራ የቆየው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጪው ቅዳሜ ጥቅምት 14 በይፋ ስራውን እንደሚያጠናቅቅ ገልጿል።
ኮሚሽኑ በስራ በቆየባቸው ጊዜያት 4 ሺህ ተሳታፊዎች የተገኙበት የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተካሂዶ የተሰበሰቡ 400 ገደማ ምክረ ሀሳቦች ይፋ መደረጋቸው ይታወሳል።
በሀገራዊ ምክክሩ ለሀገረ መንግሥት ግንባታና ለዲሞክራሲ ሥርዓት መዳበር መሰረት የሚሆኑ ጠቃሚ ምክረ ሀሳቦች መገኘት መቻላቸውም ተጠቁሟል፡፡
